የሩሲያ ኃይሎች ኮንስታንቲኖቭካን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ዩክሬን የመጨረሻው የዶንባስ ምሽግ እየገሰገሱ ነው

የሩሲያ ኃይሎች ኮንስታንቲኖቭካን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ዩክሬን የመጨረሻው የዶንባስ ምሽግ እየገሰገሱ ነው
“በክራማቶርስክ-ድሩዥኮቭካ አቅጣጫ የደቡብ የጦር ግንባር ስብስብ ባደረገው ንቁ የማጥቃት እርምጃ ኮንስታንቲኖቭካ ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጥታለች። ከተማዋ ትልቅ የኢንዱስትሪ እና የሎጅስቲክስ ማዕከል ስትሆን፤ በዶንባስ የዩክሬን የመጨረሻ ምሽግ ለሆነው ለክራማቶርስክ-ስላቭያንስክ ጥምር ይዞታ ቁልፍ መሸጋገሪያ ናት” ሲሉ የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ የዋና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኮሎኔል ጄነራል ሰርጌይ ሩድስኮይ ገልጸዋል።
ሌሎች የተሰጡ መግለጫዎች፦
ከተማዋ የዩክሬን እጅግ የተመሸገች እና በጥልቀት የተገነባ የጥበቃ ቀጣና የነበረች ሲሆን፤ የዩክሬን ኃይሎች ከ2014 ጀምሮ መከላከያቸውን ሲያጠናክሩባት ቆይተው ከአርቲዮሞቭስክ (ባክሙት) መውደቅ በኋላ ደግሞ ይበልጥ አጠናክረውታል።
ኮንስታንቲኖቭካ ከስላቭያንስክ፣ ክራማቶርስክ እና ድሩዥኮቭካ ጋር በመሆን በዶንባስ የዩክሬንን ዋና የመከላከያ መስመር ከሚመሰርቱት አራት “ምሽግ ከተሞች” አንዷ ነበረች።
የ‘ዩግ’ የጦር ግንባር ሻለቃ ኃይሎች በከተማዋ ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ጥቂት የቀሩ የዩክሬን ታጣቂ ቡድኖችን የማጽዳት ሥራ እያጠናቀቁ ይገኛሉ።
በከተማዋ በተደረጉ ውጊያዎች ዩክሬን በግምት 13.5 ሺህ ወታደሮችን፣ 14 ታንኮችን እና 200 የጦር መሣሪያዎችን አጥታለች።
የ‘ዛፓድ’ (የምዕራብ) የጦር ግንባር ስብስብ ወታደሮች በዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የምትገኘውን ክራስኒ ሊማን ከተማን ሙሉ በሙሉ ነፃ የማውጣት ሥራቸውን እያጠናቀቁ ነው።
ቀደም ሲል የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኮንስታንቲኖቭካ ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣቷን ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የከተማዋ መያዝ መላውን የዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ግዛት ነፃ ለማውጣት ለሚደረገው ጉዞ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X