ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ዕዝ መሪነትን ለኬንያ አስረከበች
14:45 04.07.2026 (የተሻሻለ: 14:54 04.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ዕዝ መሪነትን ለኬንያ አስረከበች
ላለፉት ሦስት ዓመታት የኃይሉ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት ኢትዮጵያዊው ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው አሊ፤ ዕዙን ለኬንያዊው ብርጋዲየር ጄኔራል ስቴፈን ማይና ሁሪያ ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።
በርክክቡ ላይ ንግግር ያደረጉት ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው አሊ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተጠንቀቅ ኃይሉን ዝግጁነት ከማጠናከር ባለፈ በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ቅንጅት ማሳደግ መቻሉን ገልጸው, ኃላፊነት ለሰጣቸው ለኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር እና ለድርጅቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አዲሱ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል አዛዥ ኬንያዊው ብርጋዲየር ጄነራል ስቴፈን ማይና ሁሪያ በበኩላቸው፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/5
© telegram sputnik_ethiopia

2/5
© telegram sputnik_ethiopia

3/5
© telegram sputnik_ethiopia

4/5
© telegram sputnik_ethiopia

5/5
© telegram sputnik_ethiopia
1/5
© telegram sputnik_ethiopia
2/5
© telegram sputnik_ethiopia
3/5
© telegram sputnik_ethiopia
4/5
© telegram sputnik_ethiopia
5/5
© telegram sputnik_ethiopia