የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ

የዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በቤንዚን የሚንቀሳቀስ የ”ሳንድስቶርም ኤስ24 ፒክአፕ” ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ በተሳካ ሁኔታ መቀየሩ ተገለጿል። ይህ በዩኒቨርሲቲው የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ተመራማሪዎች የተሠራው ፕሮጀክት ለሁለት ዓመት በምርምር የቆየ ሀገራዊ ተነሳሽነት መሆኑን የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ኢዶሳ ቱፋ አስረድተዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ዶክተር ታጠቅ ማሞ የጠቀሷቸው ዋና ዋና ቴክኒካዊ ዝርዝሮች እና ጥቅሞች፦

70 ኪሎዋት ፒኤማኤሳኤም (PMSM) ኤሌክትሪክ ሞተር፣ 65 ኪሎዋት ሰዓት ሊቲየም-አዮን ባትሪ እና “ሪጄኔሬቲቭ ብሬክ” ሥርዓት ተገጥሞለታል።

በአንድ ቻርጅ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ይጓዛል፤ ዜሮ የጭስ ልቀት አለው።

የአሠራር ወጪን በ88 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ወጪ ከ4 እስከ 5 ዓመታት ውስጥ መመለስ ይችላል።

ኘሮጀክቱ በአጠቃላይ አንድ ዋና ተመራማሪ እና አምስት ቴክኒካል ቡድን የተዋቀረ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቤንዚን ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0