የሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ እና የናይጄሪያዋ ኒጀር ግዛት አዲስ ኢኮኖሚያዊ እና ሳይንሳዊ ትስስር ለመፍጠር የትብብር ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ - መግለጫ
12:55 04.07.2026 (የተሻሻለ: 13:04 04.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ እና የናይጄሪያዋ ኒጀር ግዛት አዲስ ኢኮኖሚያዊ እና ሳይንሳዊ ትስስር ለመፍጠር የትብብር ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ - መግለጫ
የሩሲያዋ ከተማ በሃይል፣ በማዕድን፣ በግብርና፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማሳደግ በቆዳ ስፋቷ ትልቅ ከሆነችው የናይጄሪያ ግዛት ጋር አጋርነት መመሥረቷን የሴንት ፒተርስበርግ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አስታውቋል።
የከተማዋ አስተዳዳሪ አሌክሳንደር ቤግሎቭ እና የኒጀር ግዛት ገዥ መሐመድ ኡማሩ ባጎ ወደፊት በጋራ ሊከናወኑ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የሩሲያ የግብርና ማሽነሪዎችን ማቅረብ፣
የሕክምና ማዕከል መገንባት፣
የጂኦሎጂካል ምርምር ማዕከል ማቋቋም እና
በናይጄሪያ ውስጥ የሴንት ፒተርስበርግ የንግድ ማዕከል መክፈት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X