ሩሲያ እና ታንዛኒያ የቱሪዝም ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ታንዛኒያ የቱሪዝም ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱ የተፈረመው ከዳሬሰላም ወደ ሞስኮ የተደረገውን የመጀመሪያውን ቀጥታ በረራ ተከትሎ መሆኑን የሩሲያ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ረሼትኒኮቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።

ይህ በረራም በሰኔ ወር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የተደረገው ስብሰባ ውጤት መሆኑን ሚኒስትሩ አክለው አብራርተዋል።

ሁለቱ ሀገራት የጋራ የሥራ ቡድኖችን እንደሚያቋቁሙና ስምምነቱን በፍጥነት ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችል የሦስት ዓመት የድርጊት መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጁ የታንዛኒያ ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር አሻቱ ካችዋምባ ኪጃጂ ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ ለስፑትኒክ አፍሪካ ሲናገሩም፣ “የታንዛኒያ መዳረሻዎችን እና የሩሲያን መዳረሻዎችን በጋራ ማስተዋወቅ አለብን” ብለዋል።

ለዝርዝር መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0