ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እና ጀማሪ አዳዲስ አትሌቶች በኡጋንዳው “ሩዌንዞሪ ማራቶን” ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ
19:45 03.07.2026 (የተሻሻለ: 19:54 03.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እና ጀማሪ አዳዲስ አትሌቶች በኡጋንዳው “ሩዌንዞሪ ማራቶን” ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ
ይህ ተነሳሽነት ኢትዮጵያና ኡጋንዳን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ በሆኑ የጎዳና ላይ ሩጫዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የስፖርት ቱሪዝምን ለማሳደግና የጎረቤት አገራትን የስፖርት ማኅበረሰብ ይበልጥ ለማስተሳስር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓለም አትሌቲክስ ደረጃ ዕውቅና ያለው ይህ የማራቶን ውድድር፦
በምዕራብ ኡጋንዳ ካሴሴ ከተማ የሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
ሙሉ ማራቶን (42 ኪ.ሜ)፣ ግማሽ ማራቶን (21 ኪ.ሜ)፣ የ10 ኪ.ሜ እና የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫዎችን ያካተተ ነው፡፡
ይህ ግብዣ የቀረበው ቅዳሜ በአዲስ አበባ እንጦጦ ፓርክ ከሚካሄደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሩጫ ውድድር ቀደም ብሎ ሲሆን፤ ፍላጎት ያላቸው ሯጮች በማራቶኑ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ መመዝገብ እንደሚችሉ ተዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X