ከቡና የውጭ ንግድ የተገኘው 3 ቢሊዮን የአማሪካ ዶላር ገቢ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የከፈተ ነው - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
18:15 03.07.2026 (የተሻሻለ: 18:24 03.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከቡና የውጭ ንግድ የተገኘው 3 ቢሊዮን የአማሪካ ዶላር ገቢ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የከፈተ ነው - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
ጥራትን ማዕል ያደረጉ ተግባራት ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ በታሪክ ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ ማስቻሉን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በቡና የወጪ ንድድ የተገኘውን ስኬት አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቡና የውጭ ንግድ 3 ቢሊዮን የአማሪካ ዶላር ገቢ በማስመዝገብ አዲስ የእድገት ምዕራፍ ከፍታለች። ይህ ስኬት ዝም ብሎ የተገኘ ሳይሆን ዓለም አቀፉ የቡና ገበያ በከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ እና እስከ 40 በመቶ በሚደርስ የዋጋ ማሽቆሎቆል ውስጥ ባለበት አስቸጋሪ ወቅት የተመዘገበ ተአምር ነው።" ብለዋል።
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለቡና የወጪ ንግድ እድገት የፈጠራቸውን እድሎች ለመጠቀም ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ወደ ቻይና የሚላከው የቡና መጠን በእጅጉ መጨመሩን እና ወደ ሩሲያ የሚላከውን ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X