የሩሲያ-ታንዛኒያ የቀጥታ በረራ መስመር በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያጠናክራል - የትራንስፖርት ሚኒስትሩ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ-ታንዛኒያ የቀጥታ በረራ መስመር በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያጠናክራል - የትራንስፖርት ሚኒስትሩ

የቀጥታ በረራዎች መጀመር አስቀድመው “በባህል፣ በትምህርት እና በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን እያጠናከሩ ባሉት” በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጭነት ማጓጓዣ (ካርጎ) ያሳድጋል ሲሉ የታንዛኒያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ማካሜ ምንያ ምባራዋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ሲያብራሩም፣ “ታንዛኒያ የግብርና ሀገር ናት፤ እዚህ ሞስኮም ሆነ በአጠቃላይ በሩሲያ እንደ ፍራፍሬዎች በተለይም አቮካዶ  እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ፍላጎት አለ” በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለምሥራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ይህ ትብብር “ከፍተኛ ዕድገት ለማስመዝገብ” እንደ ሩሲያ ካሉ የበለጸጉ ሀገራት ብዙ ለመማር ዕድል እንደሚፈጥርላት ምባራዋ በማጠቃለያቸው ጠቅሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0