ታንዛኒያ ቀጥታ በረራዎች በመጀመራቸው በየዓመቱ 500 ሺህ ሩሲያውያን ጎብኚዎችን ለመሳብ ግብ አስቀምጣለች - የቱሪዝም ሚኒስትር
16:15 03.07.2026 (የተሻሻለ: 16:24 03.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ ቀጥታ በረራዎች በመጀመራቸው በየዓመቱ 500 ሺህ ሩሲያውያን ጎብኚዎችን ለመሳብ ግብ አስቀምጣለች - የቱሪዝም ሚኒስትር
በሞስኮ እና በዳሬ ሰላም መካከል ቀጥታ በረራዎች መጀመራቸውን ተከትሎ፣ በዚህ ዓመት ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የሚያቀኑ የሩሲያ ጎብኚዎች ቁጥር በብዙ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዶ/ር አሻቱ ካችዋምባ ኪጃጂ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. በ2025 ታንዛኒያ 17,100 ሩሲያውያን ጎብኚዎችን መመዝገቧን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።
"ሆኖም፣ በሩሲያእስከ 20 ሚሊዮን የሚደርሱ ወደ ውጭ ሀገራት የሚሄዱ ተጓዦች እንዳሉ እናውቃለን። ስለዚህም ዛሬ ከዳሬ ሰላም ተነስቶ እዚህ ሩሲያ ከደረሰው ቀጥታ በረራ ጋር ተያይዞ ይህ ቁጥር ይጨምራል ብለን እናምናለን" ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት የቱሪዝም ትብብር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የጋራ የሥራ ቡድኖችን እንደሚያቋቁሙና ስምምነቱን በፍጥነት ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችል የሦስት ዓመት የድርጊት መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጁ የታንዛኒያ ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር አሻቱ ካችዋምባ ኪጃጂ ገልጸዋል።
የትኞቹ መዳረሻዎች ለሩሲያውያን ጎብኚዎች የበለጠ ሳቢ ይሆናሉ የሚለውን ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X