በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በጥንቃቄ እና በኃላፊነት ስሜት መጠቀም እንደሚገባ ባለሙያዎች አሳሰቡ

ሰብስክራይብ

በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በጥንቃቄ እና በኃላፊነት ስሜት መጠቀም እንደሚገባ ባለሙያዎች አሳሰቡ

የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬስብሃት፣ ቴክኖሎጂው በሙዚቃ ሥራ ላይ ጊዜን እና ልፋትን የሚቀንስ ቢሆንም፣ ዋናው የፈጠራ ሥራ ግን በሰው ልጅ መከናወን እንዳለበትና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን እንደ ረዳት መሣሪያ ብቻ መጠቀም እንደሚቻል መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የሙዚቃ ጥናት ባለሙያ መድህን ተሰማ በበኩላቸው፣ ሙዚቀኞችና የጥበብ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂውን ውጤቶች በሚጠቀሙበት ወቅት የራሳቸውን መሠረታዊ የፈጠራ ክህሎት ማዕከል ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የሥነ ጥበብ ዕድልና ፈተናዎች” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የፓናል ውይይት መድረክ ላይ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች ከቪዲዮው ይመልከቱ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0