የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሁለት አይነት አሰራር፦ ሒሳብ ቀመር እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በፍርድ ቤቱ አፍሪካ ላይ ያለውን መዋቅራዊ አድልዎ እንዴት እንዳጋለጡ ቤኒናዊው ሳይንቲስት ይፋ አደረጉ
የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሁለት አይነት አሰራር፦ ሒሳብ ቀመር እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በፍርድ ቤቱ አፍሪካ ላይ ያለውን መዋቅራዊ አድልዎ እንዴት እንዳጋለጡ ቤኒናዊው ሳይንቲስት ይፋ አደረጉ
የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቋንቋ ትንተና እንደሚያሳየው፤ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለአፍሪካ ግጭቶች ስሜት ቀስቃሽ ቃላትን ሲጠቀም፣ ከአፍሪካ ውጪ ላሉት ግን ደረቅና ቴክኒካዊ ቃላትን በመጠቀም ግልጽ የሆነ ሁለት አይነት (ድርብ) አሰራር እያሳየ መሆኑን የሒሳብ ቀመር ሊቅና የዳታ ሳይንቲስት የሆኑት ዶ/ር ሁአንክፖ ሄክተር ጊብሰን ኪንማንሆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ይህ ግኝት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት (ከ2002 እስከ 2022) የፍርድ ቤቱ አብዛኛዎቹ ምርመራዎች በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸውን ከሚያሳየው የስታቲስቲክስ እውነታ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚገጣጠም መሆኑን ጠቁመዋል።
የመረጃ አስፈላጊነት
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ ዘመናዊው የተፈጥሮአዊ ቋንቋ ሂደት ቴክኖሎጂ እነዚህን የትርክት አለመመጣጠኖች በተጨባጭ መገምገም እና ማጋለጥ የሚችል ሲሆን፤ ይህም ለልዩነቱ የማይካድና በመረጃ የተደገፈ ማረጋገጫ ይሰጣል።
አፍሪካ ምን ማድረግ ትችላለች?
ይህንን የፍትሕ መጓደል ለመታገል የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታል ሉዓላዊነታቸውን በማረጋገጥ እና የራሳቸውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በማበልጸግ የቴክኖሎጂ "ውጊያውን" ማሸነፍ እንዳለባቸው ኪንማንሆን በማጠቃለያቸው ጠቅሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X