የሩሲያ አዲሱ የሚሳኤል ናዳ ታክቲክ ዩክሬን ሰላም እንድትሻ ሊያስገድዳት ይችላል – ወታደራዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ አዲሱ የሚሳኤል ናዳ ታክቲክ ዩክሬን ሰላም እንድትሻ ሊያስገድዳት ይችላል – ወታደራዊ ባለሙያ

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፤ የሀገሪቱ ጦር በዩክሬን የነዳጅ እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት አውታሮች እንዲሁም በፍላሚንጎ ሚሳኤል እና የድሮን ማምረቻ ፋብሪካዎች ላይ ሰፊ ጥቃት ማካሄዱን አስታውቋል።

​ሰኔ 25 የተካሄደው ጥቃት የክሩዝ፣ ሱፐርሶኒክ እና ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎችን ጥምረት በመጠቀም በከፍተኛ ትክክለኛነት በሚዋጉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተደገፈ ነበር።

​ከዘለንስኪ የተደናገጠ ምላሽ መገመት እንደሚቻለው በፍላሚንጎ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ እንደነበር ነው ሲሉ የወታደራዊ-ፖለቲካዊ ትንተና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አሌክሳንደር ሚካይሎቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ በአውሮፓ የተሠሩ የጦር መሣሪያዎች "የምርት መስተጓጎል ያጋጥማቸዋል"፣

​ "ዩክሬን ላይ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ከአሁን በኋላ ምንም ዓይነት ገደብ እይኖርም፤ በዚህ ምክንያት ከዚህ በኋላ የሩሲያ ጦር ኃይሎች የትኛውንም ወታደራዊ ዒላማ መምታት ይችላሉ።"

​ በዩክሬን የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የተሰነዘሩት የሩሲያ ጥቃቶች የዩክሬን ወታደራዊ ሎጅስቲክስንም ያሰናክላሉ።

​"ዩክሬን በግዛቷ ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለማስቆም ሁሌም አማራጭ አላት። ቅድመ ሁኔታዎቹንም በሚገባ ታውቃለች" ሲሉ ሚካይሎቭ አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0