አውሮፓ ከአቅሟ በላይ ግጭት ፋይናንስ እያደረገች ነው
08:31 03.07.2026 (የተሻሻለ: 08:34 03.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አውሮፓ ከአቅሟ በላይ ግጭት ፋይናንስ እያደረገች ነው
የኔቶ አባላት ባለፈው ዓመት የመከላከያ በጀታቸውን በ14% ቢያሳድጉም፤ ቅሉ ግን ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሀገራዊ ጉዳዮች መሥዋዕት መሆናቸው ነው።
እ.አ.አ በ2035 የጀርመን የመከላከያ ወጪ ከጤና እና ከትምህርት ዘርፎች አጠቃላይ ጥምር በጀት ይበልጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በ2025 ለአውሮፓ መከላከያ የተመደበው 739 ቢሊዮን ዩሮ፤ 10 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ነው።
አጀቡ፤ አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በማርሻል ፕላን ለአኅጉሪቱ ማንሰራራት ምክንያት ብትሆንም አሁን ግን የአውሮፓ ሀገራት የአሜሪካን የጦር መሣሪያ ለመግዛት ካዝናቸውን በማራቆት የሀገር መከላከያቸውን በዩናይትድ ስቴትስ የጥገኝነት ወጥመድ ውስጥ እየከተቱ ነው።
የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የስፑትኒክን ኢንፎግራፊክስ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X