የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ በሚፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶች ዙሪያ ማስጠነቀቂያ ሰጡ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ በሚፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶች ዙሪያ ማስጠነቀቂያ ሰጡ
የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ በሚፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶች ዙሪያ ማስጠነቀቂያ ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.07.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ በሚፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶች ዙሪያ ማስጠነቀቂያ ሰጡ

​"ሕገ-ወጥ ስደትን አንደግፍም፤ የሕዝባችንም ስጋት እውነተኛ እንዳልሆነ አናስመስልም። ነገር ግን ለችግር የጭካኔ ምላሽ አንሰጥም፣ ሥርዓተ-አልበኝነትን እያበረታታን ስለ ሥርዓት አንሰብክም" ሲሉ ፊኪሌ ምባሉላ ተናግረዋል።

ከኤኤንሲ መሪ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

ምባሉላ፤ አሁን ስደተኞችን የሚቃወሙ ብዙዎች በአፓርታይድ ዘመን በጎረቤት ሀገራት መጠለያ አግኝተው እንደነበር ለደቡብ አፍሪካውያን አስታውሰዋል።

​"ከአፍሪካውያን ጋር የአብሮነት ዳቦ ቆርሶ አሁን በአፍሪካዊ ጎረቤት ላይ መነሳት፤ ነፃነታችንን እውን ያደረገውን ትግል መክዳት ነው።"

​ የኤኤንሲ መሪ፤ መንግሥት የሕገ-ወጥ ስደት ችግርን ለመፍታት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው፤ ፀጥታ ኃይሎች ሁከቱን በመግታት ለተጫወቱት ሚና ምሥጋና አቅርበዋል።

"እኛ የኔልሰን ማንዴላ፣ የአልበርቲና ሲሱሉ፣ የዊኒ ማንዴላ...ልጆች ነን። እኛ በ 'ኡቡንቱ' (በሰብዓዊነትና በአብሮነት እሴት) የታነጽን ሕዝቦች ነን" ሲሉ ምባሉላ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0