የሳኅል ሀገራት ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጋር ተለያየ

© telegram sputnik_ethiopiaየሳኅል ሀገራት ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጋር ተለያየ
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጋር ተለያየ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.07.2026
ሰብስክራይብ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጋር ተለያየ

ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ኒጀርን በመከተል ከአይሲሲ መውጣታቸውን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በይፋ አሳውቀዋል።

ሦስቱ የኤኢኤስ ሀገራት ተቋሙ ለፖለቲካዊ ዓላማዎችና አዲስ የቅኝ አገዛዝ ጭቆና ማገልገያ እየሆነ ነው በሚል ከፍርድ ቤቱ እንደሚወጡ ያስታወቁት እ.አ.አ በመስከረም ወር 2025 የነበረ ሲሆን በምትኩም ክልላዊ የሳኅል ፍርድ ቤት ለማቋቋም ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

ውሳኔውን የተመለከቱ ዋና ዋና ጉዳዮች፦

የሚጸናበት ቀን፦ ከፍርድ ቤቱ የመውጣት ሂደቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን ለኒጀር እ.አ.አ ሰኔ 18 ቀን 2027፤ ለማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ደግሞ ሰኔ 24 ቀን 2027 ይሆናል።

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ምላሽ፦ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ማዘኑን ገልጾ፤ ሀገራቱ ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑት እና በአይሲሲ የፈራሚ ሀገራት ጉባኤ ማዕቀፍ ውስጥ ገንቢ ውይይቶችን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ውጤት፦ በጉባኤው ውስጥ ያለው የአፍሪካ ቡድን አባልነት ቁጥር ከ33 ወደ 30 ዝቅ ይላል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0