በጀርመን የፑሽኪን መታሰቢያ ሐውልት ስርቆት"የባሕል ስረዛ" አካል ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
17:25 02.07.2026 (የተሻሻለ: 19:11 02.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በጀርመን የፑሽኪን መታሰቢያ ሐውልት ስርቆት "የባሕል ስረዛ" አካል ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
በጀርመን ሰሜን ራይን-ዌስትፋሊያ ግዛት ሄመር ከተማ የሚገኘው የሩሲያዊው ገጣሚና ጸሐፊ የነሐስ መታሰቢያ ሐውልት መዘረፉን፤ በጀርመን የሩሲያ ኤምባሲ በትናንትናው ዕለት አስታውቋል።
ማሪያ ዛካሮቫ፤ “ይህ ‘የመሰረዝ ባሕል’ የባሕል እጦትን ብቻ ሳይሆን ሰው ጠል ርዕዮተ ዓለምን እንደሚያቀጣጥል ከአውሮፓውያን ውጪ ሌላ ማን ሊያውቅ ይችላል?” ሲሉ በቴሌግራም ቻናላቸው ባጋሩት ጽሁፍ አስገንዝበዋል።
ቃል አቀባይዋ አክለውም፤ በፖላንድ እና በባልቲክ ሀገራት ባለሥልጣናት አውሮፓን ነፃ ባወጡ የቀይ ጦር ወታደሮች መታሰቢያ እና የመቃብር ስፍራዎች ላይ የተከፈተው “የሐውልቶች ጦርነት” አሁን ወደ ጀርመን ተዛምቷል ብለዋል።
ቁመቱ በግምት 1.8 ሜትር የሚሆነው የፑሽኪን የነሐስ ሐውልት፤ በሩሲያዊው ቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ግሪጎሪ ፖቶትስኪ ተሠርቶ፤ የሄመር እህት ከተማ በሆነችው የሩሲያዋ ሽቼልኮቮ ከተማ የተበረከተ ነበር። በሩሲያ እና በጀርመን ሕዝቦች መካከል የጋራ መግባባት እና የወዳጅነት ምልክት እንዲሆን ታስቦ የቆመው ይህ ሐውልት፤ ይፋዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው እ.አ.አ መስከረም 24፣ 1994 ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X