ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ ፕሮቶኮላቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር ተስማሙ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ ፕሮቶኮላቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር ተስማሙ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ፤ ከደቡብ ሱዳን የፒቦር ልዩ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ቦዮይ ጎላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ፕሮቶኮሉ የሁለቱን ሀገራት የድንበር ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ማዕከል ያደርገ እንደሆነ ገልጸዋል።

 

እንደ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ሁለቱ ኃላፊዎች ከታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ዙሪያም ተወያይተዋል፦

▪ ሕገ-ወጥ የድንበር ንግድን ስለመግታት፣

▪ መደበኛና ሕጋዊ የኢኮኖሚ አጋርነት ስለመፍጠር፣

▪ ስለድንበር ደኅንነት።

 

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ ፕሮቶኮሉን ወደ ትግበራ ለማሸጋግር ቁርጠኝነታቸውን በመግለጽ ውይይታቸውን እንዳጠናቀቁ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0