በ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠ ግለሰብ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ

© telegram sputnik_ethiopiaበ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠ ግለሰብ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ
በ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠ ግለሰብ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.07.2026
ሰብስክራይብ

በ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠ ግለሰብ ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ

​ የጀርመን ባለሥልጣናት በቱትሲዎች ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፎ አለው ተብሎ የተጠረጠረና የጀርመን-ሩዋንዳ ዜግነት ያለውን ግለሰብ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር አውለዋል።

​ግለሰቡ በአምስት የተለያዩ አጋጣሚዎች የ25 ቱትሲዎችን ግድያ አዟል በሚል የተከሰሰ ሲሆን በአንዱ ግድያ ደግሞ ራሱ የአንድን ሰው ደረት በስለት በመውጋት በግንባር ቀደምትነት በወንጀሉ መሳተፉ ተገልጿል።

​ በሰሜን ምዕራብ ሩዋንዳ የአንድ ወረዳ መሪ ረዳት ሆኖ በሰራበት ወቅት፤ ሥልጣኑን ተጠቅሞ ግድያዎችን በመቀስቀስ፣ የሚገደሉ ሰዎችን ዝርዝር በማዘጋጀት እና በቱትሲ ተወላጆች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን በማስተባበር ተጠርጥሯል።

​የጀርመን ዓቃቤ ሕግ ግለሰቡን በዘር ማጥፋት ተባባሪነት እና በበርካታ የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች ለመክሰስ የሚያስችል በቂ ማስረጃ መኖሩን አስታውቋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0