የኔታንያሁ የጋዛ የማፈናቀል ዕቅድ እስራኤል የፍልስጤምን ይዞታ የመያዝ ዓላማ እንዳላት ያሳያል - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የኔታንያሁ የጋዛ የማፈናቀል ዕቅድ እስራኤል የፍልስጤምን ይዞታ የመያዝ ዓላማ እንዳላት ያሳያል - ባለሙያ

​እስራኤል ሶማሊላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሊቢያ የጋዛ የፍልስጤም ስደተኞችን እንዲቀበሉ ጠይቃ፤ ሁሉም ሀገራት ሐሳቡን ውድቅ እንዳደረጉት ወይም ምንም ዓይነት ስምምነት አለመኖሩን እንዳስተባበሉ ተዘግቧል።

​“ይህ እስራኤል በፍልስጤም ሕዝብ የተያዙትን እና የምትቆጣጠራቸውን ግዛቶች ለማስፋፋት የምትከተለው ፖሊሲ ነው" ሲሉ በአንካራ የፀጥታና የፖለቲካ ተንታኝ ሰሊም ኦዘርተም ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ ከጋዛ የሚደረግ ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰት “የሥልጣን ክፍተት” ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

​ እንዲሁም እስራኤል ግዛቱን ወደ ራሷ ማጠቃለሏ በአረብ መሪዎችና ዜጎች ዘንድ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው ገልጸዋል።

​ ስደተኞችን መቀበል “የሥራ ስምሪት፣ የጤና እና የማኅበራዊ ዋስትና ችግሮች የሚጋፈጡ ሰዎችን እና አዳዲስ ባሕሎችን መቀበል ማለት ነው።”

ኦዘርተም አክለውም፤ “እስራኤል በጋዛ ወታደራዊ ጫና ባማድረስ፤ የቀጣናውን የሥነ-ሕዝብ ስብጥር ለመቀየር አማራጭ መፍትሔዎችን እየፈለገች ነው” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0