የአፍሪካ ልማት ባንክ እየቀነሰ የመጣውን የቻድ ሐይቅ ለመታደግ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ልማት ባንክ እየቀነሰ የመጣውን የቻድ ሐይቅ ለመታደግ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ
የአፍሪካ ልማት ባንክ እየቀነሰ የመጣውን የቻድ ሐይቅ ለመታደግ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.07.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ልማት ባንክ እየቀነሰ የመጣውን የቻድ ሐይቅ ለመታደግ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

​በባንኩ እና በቻድ ሐይቅ ተፋሰስ ኮሚሽን የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት፤ የተፋሰሱን ሥነ-ምህዳራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ወደ ነበረበት በመመለስ፤ በሐይቁ ሀብት የሚተዳደሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ኑሮ ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ የአፍሪካ ልማት ባንክ መግለጫ አመልክቷል።

የፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ትኩረቶች፦

ቴክኒካዊ ጥናቶች፣

የውሃ ሞዴሊንግ (የውሃ ፍሰት እና አቅርቦት ትንበያ)፣

ለጎርፍ እና ለድርቅ የሚያገለግል ቀጣናዊ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ሥርዓት።

እነዚህ መሣሪያዎች ለወደፊት ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች መሠረት ይጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ የመጨረሻ ግቦች የሚከተሉት ናቸው፦

የአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋዎችን መቋቋም፣

የምግብ ዋስትናን ማሳደግ፣

ከ40 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የሚኖሩበትን ቀጣና መረጋጋት ማገዝ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0