ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምታካሂደው የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ መጨመሩ ተገለጸ
19:46 01.07.2026 (የተሻሻለ: 19:54 01.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምታካሂደው የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ መጨመሩ ተገለጸ
ሀገሪቱ እ.አ.አ በ2025 940 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ለአፍሪካ ሀገርት መላኳን አፍሪኤግዚም ባንክ ባወጣው የንግድ ሪፖርት አመልክቷል።
ይህም እ.ኤ.አ 2024 ከተመዘገበው 540 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 75 በመቶ ገደማ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከአፍሪካ ሀገራት ከገባው 1.19 ቢሊዮን ዶላር የገቢ ንግድ መጠን ጋር ተዳምሮ አኅጉራዊ የንግድ ልውውጥ 2.13 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
ሆኖም ቀጣናዊ የንግድ ልውውጡ ከሀገሪቱ የ25 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የሚሸፍነው ከሁለት በመቶ በላይ ብቻ ነው መባሉን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X