ቡሩንዲ የሴት ተማሪዎችን እኩል የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ነው - ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ቡሩንዲ የሴት ተማሪዎችን እኩል የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ነው - ሚኒስትር

​ ሴት ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያላቸውን ቆይታ ለማሻሻል፤ ሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲዎችን የምግብ አቅርቦት መልሳ እያደራጀችና የተማሪ መኖሪያዎችን እየገነባች መሆኑን የብሩንዲ የብሔራዊ ትምህርት እና ሳይንሳዊ ምርምር ሚኒስትር ፍራንስዋ ሀቭያሪማና ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የሀብት እጥረት ሥራውን መቶ በመቶ ስኬታማ ለማድረግ ማነቆ እንደሆነ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።

​ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት፤ በነገው ዕለት በቡሩንዲ መዲና ከሚጀመረውና በአፍሪካ ኅብረት አዘጋጅነት ለሁለተኛ ጊዜ ከሚካሄደው የሴት ልጆች እና የሴቶች ትምህርት የፓን-አፍሪካ ጉባኤ ዋዜማ በሰጡት መግለጫ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0