የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ማክሰኞ ዕለት ለተደረጉት ሰላማዊ የፀረ-ስደተኞች ሰልፎች ዜጎችን አደነቀ
18:22 01.07.2026 (የተሻሻለ: 18:24 01.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ማክሰኞ ዕለት ለተደረጉት ሰላማዊ የፀረ-ስደተኞች ሰልፎች ዜጎችን አደነቀ
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ዜጎች፤ ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆኑ ከስደት ጋር የተያያዙ ሰልፎችን ማካሄዳቸውን አድንቆ፤ በድንበር ደህንነት፣ በኢኮኖሚ እና ከሕዝብ ሰላም ጋር ተያይዞ ያነሷቸውን መሠረታዊ ስጋቶች እንደሚጋራም በመግለጫው ጠቅሷል።
የፕሬዚዳንቱን የስደት ስትራቴጂ በድጋሚ በማረጋገጥ፤ የሚከተሉትን ለማድረግ ቃል ገብቷል፦
የኢሚግሬሽን እና የሠራተኛ ሕጎችን በጥብቅ ማስከበር፣
ድንበሮችን አስተማማኝ ማድረግ፣
መደበኛ ካልሆነ ስደት ጋር በተያያዙ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ።
መንግሥት በተጨማሪም ሕዝቡ መጤ ጠልነትን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ውድቅ እንዲያደርግ እንዲሁም ስደትን በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ለመምራት እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር አብሮ እንዲሠራ አሳስበዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ስለ ሰልፎቹ የሰጡት አስተያየት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X