ፈረንሳይ በቡርኪና ፋሶ ድንገተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የማቋረጥ ውሳኔ ተደናግጣለች ተባለ

© telegram sputnik_ethiopiaፈረንሳይ በቡርኪና ፋሶ ድንገተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የማቋረጥ ውሳኔ ተደናግጣለች ተባለ
ፈረንሳይ በቡርኪና ፋሶ ድንገተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የማቋረጥ ውሳኔ ተደናግጣለች ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2026
ሰብስክራይብ

ፈረንሳይ በቡርኪና ፋሶ ድንገተኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የማቋረጥ ውሳኔ ተደናግጣለች ተባለ

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከሩን ብታወቅም፤ ዋጋዱጉ ለፈረንሳይ ኤምባሲ መዝጊያ የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ መስጠቷ ለፓሪስ ያልተጠበቀ ውሳኔ እደሆነባት አንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ አስነብቧል።

ፈረንሳይም በተመሳሳይ በሀገሯ የሚገኙ የቡርኪና ፋሶ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖችን ለመዝጋት ማቀዷን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህ ድንገተኛ ፍቺ የቪዛ አገልግሎትን በማቋረጡ በቡርኪና ፋሶ የሚኖሩ 2 ሺህ 500 ገደማ የፈረንሳይ ዜጎች ለቆንስላ አገልግሎት የሌሎች የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት ኤምባሲዎችን እንዲጠቀሙ ማስገደዱን መገናኛ ብዙኃን አንድ የፈረንሳይ ዲፕሎማትን ዋቢ አድርገው አመልክተዋል።

ቡርኪና ፋሶ ፈረንሳይን በሽብርተኝነት እና ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ወንጅላ ሰኔ 19 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በይፋ አቋርጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0