የኢትዮጵያን የካርበን ገበያ በግልፅ የሕግ ማዕቀፍ የሚመራ አዋጅ ፀደቀ
17:32 01.07.2026 (የተሻሻለ: 17:34 01.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የካርበን ገበያ በግልፅ የሕግ ማዕቀፍ የሚመራ አዋጅ ፀደቀ
የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ፤ የሀገሪቱን ብሔራዊ የካርበን ገበያ ስትራቴጂ ወደ ትግበራ የሚያስገባ ነው ተብሏል።
በፓርላማ በቀረበው ማብራሪያ መሠረት የአዋጁ ዓላማ፦
▪ አረንጓዴ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣
▪ የካርቦን ክሬዲትን መቆጣጠር፣
▪ ግልጽ የሆነ የገቢ ክፍፍልን ማረጋገጥ ነው።
አዋጁ የካርበን ግብይት ሂደትን በተበታተነ መልኩ ሲመሩ የነበሩ ደንብና መመሪያዎችን ወደ አንድ ወጥ የሕግ ማዕቀፍ በማጠቃለል፤ ግልፅነት እና የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንደሚያሰፍን የምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ ለፓርላማው አብራርተዋል፡፡
“የፓሪሱን ስምምነት ጨምሮ ሀገራችን የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ውሎችና የገባቻቸውን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ቃል ኪዳኖች ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያግዝ አዋጅ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሰኔ 23፣ 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X