ሩሲያ ከጥር-ግንቦት 2026 ድረስ ለጋና የላከችው የዶሮ እርባታ ምርት ዘጠኝ እጥፍ በማደግ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን ኤጀንሲው ገለጸ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ከጥር-ግንቦት 2026 ድረስ ለጋና የላከችው የዶሮ እርባታ ምርት ዘጠኝ እጥፍ በማደግ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን ኤጀንሲው ገለጸ

የውጭ ንግድ ይዘቱ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

▪ የዶሮ ሥጋ እና ለምግብነት የሚውሉ ተረፈ ምርቶች (በግምት ስምንት ሺህ ቶን)፣

▪ የጅግራ ሥጋ እና ለምግብነት የሚውሉ ተረፈ ምርቶች (ከ50 ቶን በላይ)።

የሩሲያ የግብርና ኤክስፖርት ልማት ማዕከል እንደገለጸው፤ ከጥር እስከ ግንቦት ባሉት አምስት ወራት ሩሲያ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ወደ 8 ሺህ ቶን የሚጠጋ የዶሮ እርባታ ምርቶችን ለጋና ልካለች።

ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፤ በመጠን የ5.6 እጥፍ እንዲሁም በዋጋ የ9 እጥፍ ዕድገት አሳይቷል።

በአጠቃላይ ሩሲያ በተጠቀሰው ጊዜ ወደ 57 ሺህ ቶን የሚጠጋ የግብርና ምርቶችን ለጋና የላከች ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2.8 እጥፍ ብልጫ አለው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0