የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዙፋን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
12:38 01.07.2026 (የተሻሻለ: 12:44 01.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዙፋን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት ተሰርቀው ከሀገር የወጡ ከ35 በላይ ታሪካዊ ቅርሶች መመለሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።
መንግሥታቸው ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት በርካታ የጉብኝት ሥፍራዎችን ከመገንባት ባሻገር የሀገሪቱን ዋና ዋና ቅርሶች እንደጠገነም አንስተዋል።
ለአብነትም በፋሲለደስ ግንብ፣ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ በሶፍ ዑመር ዋሻ፣ በጀጎል ግንብ እንዲሁም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የተከናወኑ የእድሳት ሥራዎችን አንስተዋል።
“ቅርሶችን የምናስመልስና የምንጠብቅ እንጂ የምናፈርስ አይደለንም” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X