የሀሰን ሼክ መሀሙድ ጉብኝት በሶማሊያ ከተነሳባቸው የተቀባይነት ጥያቄ አንጻር ክልላዊ ድጋፍ ለማግኘት እያደረጉት ያለው ጥረት አካል ሊሆን ይችላል - ተንታኝ
09:30 01.07.2026 (የተሻሻለ: 09:47 01.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሀሰን ሼክ መሀሙድ ጉብኝት ሶማሊያ ውስጥ ከተነሳባቸው የተቀባይነት ጥያቄ አንጻር ክልላዊ ድጋፍ ለማግኘት እያደረጉት ያለው ጥረት አካል ሊሆን ይችላል - የቀጣናዊ ጉዳዮች ተንታኝ
የሥልጣን ዘመናቸው ግንቦት 7 ያበቃው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት፤ ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣቸው ምክንያት በሞቃዲሾ የተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊሆን እንደሚችል በደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪዋ ሰላም ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
የፌዴራል ክልሎች እና ተቃዋሚ ቡድኖች ሥልጣናቸው ላይ ጥያቄ ካነሱባቸው በኋላ ጎረቤት ሀገራትን በተከታታይ መጎብኘታቸውን ባለሙያዋ ጠቁመዋል።
"ሰኔ 22 ቀን በኬንያ ፕሬዚዳንት ሩቶን ጎብኝተው ነበር። በመቀጠል ሰኔ 26 ቀን ለጅቡቲ ብሔራዊ የነፃነት ቀን በመገኘት ፕሬዚዳንቱን ጎብኘተዋል። አሁን እዚህ አዲስ አበባም መጥተዋል። ስለዚህ ይህ የሚነግረን ነገር ፕሬዚዳንቱ ከዋና ዋና አጋሮቻቸው—ማለትም ከጎረቤት ሀገራት ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ...ተቀባይነት ለማግኘት በትክክል ጥረት እያደረጉ መሆኑን ነው።"
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በፓርላማ የፀደቀው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣንን ከአራት ወደ አምስት ዓመት በማራዘሙ ገና አንድ ዓመት እንደሚቀራቸው ይገልጻሉ። ተቃሚዎቻቸው ግን ማሻሻያው የአንድ ወገን፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ እና ሥልጣን ጨብጦ የመቆየት ዓላማቸውን ለማሳካት የተነደፈ ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X