ኢትዮጵያ በብሪክስ የልማት ባንክ መቀመጫ ማግኘቷ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ያበረታታል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ በብሪክስ የልማት ባንክ መቀመጫ ማግኘቷ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ያበረታታል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
ኢትዮጵያ በብሪክስ የልማት ባንክ መቀመጫ ማግኘቷ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ያበረታታል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በብሪክስ የልማት ባንክ መቀመጫ ማግኘቷ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ያበረታታል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

የሰሜን-ደቡብ ትብብር ታሪካዊ አዝማሚያ የደቡቡን ዓለም የዕድገት ፍላጎት ከግምት ውስጥ የማያስገባና ምዕራባውያን በሚጭኑት ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ተሾመ አዱኛ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

​"የሰሜን-ደቡብ ትብብር የደቡቡን አፋጣኝ ልማት ግምት ውስጥ ሊያስገባ አይችልም። ይልቁንም ሰሜኑ ይበልጥ እያደገ፤ ደቡቡ ደግሞ ሳያድግ የሚቀጥልበትን ነባራዊ ሁኔታ ማስቀጠል ይፈልጋል። ይህ ነባራዊ ሁኔታ መለወጥ አለበት፤ ምክንያቱም ደቡቡ ሁልጊዜ ድሃ ሆኖ የሚኖርበት ምንም ምክንያት የለም። ሰሜኑም ቢሆን ሁልጊዜ ሀብታም ሆኖ የሚቀጥልበት ምንም ምክንያት የለም።"

የፓን አፍሪካ ንቅናቄ ምልክት የሆነቸው ኢትዮጵያ፤ በባንኩ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጫ ካገኘች እያደገ ለመጣው የደቡብ-ደቡብ ትብብር እንዲሁም ለሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ኃይል እንደሚሰጥ ባለሙያው ጨምረው ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0