ሲሸልስ እና ሩሲያ የ50 ዓመት ግንኙነታቸውን በአዲስ የቱሪዝም፣ ኀዋ እና ስፖርት ትብብር አከበሩ
19:46 30.06.2026 (የተሻሻለ: 19:54 30.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሲሸልስ እና ሩሲያ የ50 ዓመት ግንኙነታቸውን በአዲስ የቱሪዝም፣ ኀዋ እና ስፖርት ትብብር አከበሩ
የሲሸልስ ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሄርሚኒ፤ በሞስኮ የሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ በቅርቡ መከፈቱን እና ሩሲያ በብሔራዊ ቀን በዓል ላይ የምታደርገውን ተሳትፎ በደስታ ተቀብለዋል።
ሩሲያ ከሶቪየት ሕብረት ዘመን ጀምሮ ስታደርግ የነበረው ድጋፍ እንዲሁም በቱሪዝም፣ በባሕር፣ ኀዋ፣ ቴክኖሎጂ እና በስፖርት አዲስ ትብብር ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗ በድጋሚ ተረጋግጧል።
የፑቲን ሰላምታ በተወካያቸው ማክሲም ኦሬሽኪን በኩል የተላለፈ ሲሆን ኦሬሽኪን የሩሲያ ገበያ ለሲሸልስ የዓሣ የወጪ ንግድ ክፍት መሆኑንም አውጀዋል።
በተጨማሪም ኦሬሽኪን ፕሬዚዳንት ሄርሚኒ በጥቅምት ወር በሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ፎረም ላይ ለመሳተፍ መወሰናቸውን አድንቀዋል።
በሌላ በኩል የሞስኮ ወታደራዊ ዲስትሪክት ተጠባባቂ አዛዥ ኢጎር ሰሪትስኪ፤ ከሲሸልስ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ስለ ትብብር የተወያዩ ሲሆን በብሔራዊ ቀኑ የሰልፍ ትርኢት ላይ እንዲገኙ ስላቀረቡላቸው ግብዣ ምሥጋና አቅርበዋል።
ℹ ሄርሚኒ ባለፈው ሚያዝያ ወር ሩሲያን የጎበኙ የመጀመሪያው የሲሸልስ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X