ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዝቅተኛ ምድብ የዕዳ ስጋት ደረጃ ለመሸጋገር ማቀዷን ገለጸች
19:09 30.06.2026 (የተሻሻለ: 19:14 30.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዝቅተኛ ምድብ የዕዳ ስጋት ደረጃ ለመሸጋገር ማቀዷን ገለጸች
ሀገሪቱ በዕዳ ሽግሽግ እና የፊስካል ማሻሻያ በሕዝብ ፋይናንስ ላይ ያለውን ጫና ማቃለል መቻሏን የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ አስታውቀዋል።
'ኢትዮጵያ ታከናውናለች' በተሰኘው ጉባኤ በሰጡት ማብራሪያ፤ "በሚቀጥለው አንድ ዓመት ገደማ ውስጥ ከመካከለኛ ወደ ዝቅተኛ የዕዳ ስጋት ደረጃ መሸጋገር እንችላለን" ማለታቸውን የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ አስነብቧል።
መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት ከውጭ የንግድ ብድር ከመውሰድ መቆጠቡንም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የዋጋ ንረትን መቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ ማድረግ፣ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲን ማዘመን እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፉን ማጠናከር እንደቻለ አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X