“ታንዛኒያ ሕገ-ወጥ ዕፆችን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች” - የታንዛኒያ ባለሥልጣን
18:34 30.06.2026 (የተሻሻለ: 18:44 30.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ታንዛኒያ ሕገ-ወጥ ዕፆችን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች” - የታንዛኒያ ባለሥልጣን
“ዛሬ ሕገ-ወጥ ዕፆች እንደ ቀድሞው በቀላሉ ወደ ታንዛኒያ አይገቡም። በዚህም ምክንያት በጎዳናዎች ዝውውራቸው በጣም ቀንሷል” ሲሉ የዕፅ ቁጥጥርና ማስከበር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አሬታስ ሊይሞ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“የመንግሥት ጠንካራ እርምጃና የፖለቲካ ቁርጠኝነት 12 ዋና ዋና የዕፅ ዝውውር መረቦችን ለመበጣጠስ” አስችሏል ብለዋል።
ይህ ስኬት የተገኘባቸውን መንገዶችም ዘርዝረዋል፦
▪ በታንዛኒያና በዓለም ሀገራት መካከል ባለው ጠንካራ ትብብር፣
▪ የሀገር ውስጥ ትብብርን በማጠናከር፣
▪ በአካባቢው ማኅበረሰብ ተሳትፎ።
ታንዛኒያ የሕገ-ወጥ ዕፆች ማጓጓዣ ዋነኛ መሣሪያ የሆነውን ጉቦ በመቆጣጠር፤ “ዋና ዋናዎቹ የዕፅ ቁንጮዎች እና የጅምላ አዘዋዋሪዎች ከእንግዲህ ወዲህ ሕገ-ወጥ ዕፆችን ወደ ታንዛኒያ ማስገባት እንደማይችሉ ማረጋገጥ ተችሏል" ብለዋል።
በታንዛኒያ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዕፅ ተጠቃሚ የሆኑበትን ምስጢር ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X