- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከዲጂታል ጥገኝነት ወደ ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ፈተና

ከዲጂታል ጥገኝነት ወደ ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ፈተና
ሰብስክራይብ
"ለእኔ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማለት ቴክኖሎጂን መግዛት ብቻ አይደለም፤ ቴክኖሎጂውን እንዴት እንደምንጠቀምበት፣ የዜጎችን ዲጂታል ሀብት እንዴት እንደምንጠብቅበት እና ማኅበረሰቡን እንዴት እንደሚያገለግል መቅረጽም ነው። […] አፍሪካ የራሷን የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ካልገነባች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቅኝ ግዛት ሰለባ የመሆን አደጋ አለ።" ሲሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሀገራት የዲጂታል ሽግግርን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ሉዓላዊነት እውን ለማድረግ የሰው ሃይልን ማብቃትን እና አስቻይ መሰረተ ልማትን መስፍጠር ወሳኝ ነው፡፡

"ገንዘብ ካለህ ቴክኖሎጂን በአንድ ሌሊት መግዛት ትችላለህ፤ ነገር ግን ዲጂታል ብቃት፣ የሰው ኃይል አቅምና ተገቢ የአስተዳደር ሥርዓት ያለ ቴክኖሎጂ በማይበቅል መሬት ላይ ዘር እንደመበተን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ከቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እንዲሁም 'የክላውድ ሴክዩሪቲ አሊያንስ ኢትዮጵያ ቻፕተር' የቦርድ አባል ከሆኑት ከአቶ እስክንድር መስፍን ጋር፣ አፍሪካ ከዲጂታል ጥገኝነት ወጥታ እውነተኛ ዲጂታል ሉዓላዊነትን እንዴት ልትገነባ እንደምትችል በስፋት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0