የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሲሸልስ ጉብኝት 19 ስምምነቶች፣ አዳዲስ ተነሳሽነቶች እና የባሕር ደህንነት ትብብር አፈራ

ሰብስክራይብ

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሲሸልስ ጉብኝት 19 ስምምነቶች፣ አዳዲስ ተነሳሽነቶች እና የባሕር ደህንነት ትብብር አፈራ

​በሲሸልስ 50ኛ ዓመት ብሔራዊ ቀን በክብር እንግድነት የተገኙት ናሬንድራ ሞዲ፤ ከፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሄርሚኒ ጋር በጤና፣ በትምህርት፣ በአቅም ግንባታ እና በባሕር ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

​የጉብኝቱ ዋና ዋና ፍሬዎች የሚከተሉት ናቸው፦

▪ ​6 የባህር ላይ ጀልባዎች እና 16 አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ለሲሸልስ መከላከያ ኃይል ተበርክተዋል፣

▪ ​500 ቶን ሩዝ እና 8 ሺህ 500 ቶን ሲሚንቶ ድጋፍ ተደርጓል፣

▪ ​ሲሸልስ የአደጋ መቋቋም መሠረተ-ልማት ጥምረትን ተቀላቅላለች።

​በተጨማሪም የሚከተሉትን ዘርፎች የሚያካትቱ 9 የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፦

▪​የጤና እንክብካቤ፣

▪​የዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ፣

▪​ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል፣

▪የባሕር ጉዞ እና አሰሳ፣

▪​የባሕር ንግድ፣

▪​የሕዋ ምርምር ትብብር።

​ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ለሲሸልስ ብሔራዊ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፤ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች "ፍትሐዊነትን፣ ኃላፊነትን እና እኩልነትን የተከተሉ" መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0