ሦስት የስዊዘርላንድ ሙዚየሞች 18 የቤኒን ነሃስ ቅርሶችን ለናይጄሪያ መለሱ

ሰብስክራይብ

ሦስት የስዊዘርላንድ ሙዚየሞች 18 የቤኒን ነሃስ ቅርሶችን ለናይጄሪያ መለሱ

​ የስዊዘርላንድ ፌዴራል መማክርት ኤልሳቤት ባውሜ-ሽናይደር እና የናይጄሪያ የጥበብ፣ ባሕልና የፈጠራ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሐናቱ ሙሳ ሙሳዋ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የሕጋዊ ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፦

▪​የሕገ-ወጥ ቅርሶች ዝውውርን መከላከል፣

▪​በሕገ-ወጥ መንገድ ከሃገር የወጡ የባሕል ቅርሶች የሚመለሱበትን መንገድ ማመቻቸት፣

▪​የመረጃ እና የሙያ እውቀት ልውውጥን ማጠናከር።

​ እነዚህ ቅርሶች በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከመዘረፋቸው በፊት ጥንታዊ መገኛቸው በነበሩት በሌጎስ እና በኤዶ ግዛት ውስጥ ለዕይታ ይበቃሉ። ከኔዘርላንድስ እና ከካምብሪጅ የተመለሱትን ቅርሶች ጨምሮ ለሁሉም ተመላሽ የቤኒን ቅርሶች አዲስ የኤግዚቢሽን ማዕከል ለመገንባት ታቅዷል።

​ታዋቂ ከሆኑት የቤኒን የነሃስ ቅርሶች መካከል የሚመደቡት እነዚህ የቤተ-መንግሥት እና የሐይማኖት መገልገያ ዕቃዎች፤ እ.ኤ.አ በ1897 ብሪታንያ በቤኒን ንጉሣዊ ግዛት ላይ ባካሄደችው ወረራ ወቅት የተዘረፉ ናቸው። በተጨማሪም፤ ስዊዘርላንድ በሕገ-ወጥ የቅርስ ዝውውር ላይ በተደረገ የፖሊስ ቁጥጥር የተያዙ ሌሎች አምስት ቅርሶችን መመለሷ ታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0