የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ እና የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የሶማሊያን የምግብ ቀውስ አባብሰውታል - የዓለም የምግብ ፕሮግራም

ሰብስክራይብ

የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ እና የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የሶማሊያን የምግብ ቀውስ አባብሰውታል - የዓለም የምግብ ፕሮግራም

"ሶማሊያ አሁንም 1.9 ሚሊዮን ሕፃናት በከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚሰቃዩባት የዓለማችን አስከፊ ቀውስ ያለባት ሀገር ሆና መቀጠሏን"፤ አዲስ ይፋ የሆነው የምግብ ዋስትና ሪፖርት እንደሚያሳያል።

ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

በሶማሊያ አሁን ላይ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በአደገኛ ረሃብ ተጠቅተዋል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል። ሰብዓዊ እርዳታ እየደረሰ ያለው ግን ለ450 ሺህ ሰዎች ብቻ በመሆኑ 76 በመቶ የሚሆነው ተረጂ ሕዝብ ያለምንም ድጋፍ ቀርቷል።

የረሃብ አደጋ በተደቀነበት በደቡብ ምዕራብ ግዛት ቡርሃካባ ወረዳ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑት ሕፃናት መካከል ወደ 40 በመቶ የሚጠጉት በከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ወይም ከዚያ በባሰ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

አነስተኛ የዝናብ መጠን፣ የማክሮ-ኢኮኖሚ ጫናዎች እንዲሁም የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ መጨመር የቤተሰቦችን የመግዛት አቅም ይበልጥ አዳክመውታል።

አሁን ላይ ወደ 60 በመቶ የሚጠጉ ቤተሰቦች መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት አይችሉም፤ ይህም ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ47 በመቶ ከፍ ያለ ነው። ይህ የዋጋ ጭማሪ እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች መሠረታዊ የምግብ ፍጆታዎችን መግዛት የማይችሉበት ስጋት ውስጥ ጥሏቸዋል።

በድርቅ፣ በግጭት፣ በጎርፍና በማፈናቀል ምክንያት የሚከሰተው ስደት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ500 ሺህ በላይ የሚሆኑት በዚሁ በ2026 የተመዘገቡ ናቸው።

የተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም፤ “የነፍስ አድን ሥራዎችን ለማስቀጠል እና የምግብ ዋስትና እጥረቱ ይበልጥ እንዳይባባስ ለመከላከል አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ወሳኝ ነው” ሲል አሳስቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0