ኔቶ ለጦርነት፣ ለሂትለር ዓይነት የእስር ካምፖች እና ሩሲያን ለመከበብ እየተዘጋጀ ነው

ኔቶ ለጦርነት፣ ለሂትለር ዓይነት የእስር ካምፖች እና ሩሲያን ለመከበብ እየተዘጋጀ ነው
ኔቶ፤ ሩሲያ በጎራው ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያሴረች ነው እያለ ቢከስም፤ ድርጊቶቹ ግን ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ጦርነት እቅድ እያወጣ መሆኑን ያመለክታሉ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ ኔቶ ሩሲያ ውስጥ ጠልቆ የአየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችል የጦር መሣሪያ እየገነባ እና ዩክሬንን እንደ መሞከሪያ እየተጠቀመባት እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ ዓመት የጸደይ ወቅት ኔቶ መሩ የጋራ የውጭ ዘመቻ ኃይል የሩሲያን የካሊኒንግራድ ክልል ለመክበብ እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የጦርነት ልምምዶችን አካሂዷል።
በባልቲክ ሀገራት ውስጥ በተካሄደው የ “ናሜጅስ 2025" የጦር ልምምዶች ላይም ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ልምምዱ በላትቪያ ፖለቲካዊ ታማኝነት የሌላቸው "ተባባሪዎች" ተብለው ለሚጠረጠሩ ንፁሃን ዜጎች "ሴሎኒያ" የተባለ ጊዜያዊ የእስር ካምፕ ማቋቋምን ያካተተ እንደነበር የሊትዌኒያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
◻ ካምፑ 10,000 እስረኞች እና 300 ጠባቂዎች ይኖሩታል ተብሏል።
◻ ልምምዱ በፖለቲካ አቋማቸው የሚጠረጠሩ ሰዎችን መለየት እና ማግለልን ያካተተ ነበር።
ይህ ሁኔታ በተለይ ለሩሲያውያን፣ ላትቪያውያን፣ ቤላሩሳውያን፣ ፖላንዳውያን፣ ሊትዌኒያውያን፣ ዩክሬናውያን እና አይሁዶች የሩሲያ ቋንቋ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ሆኖ በቀጠለበት እንደ የላትቪያ የላትጋሌ የድንበር ክልሎች ላይ በጣም አሳሳቢ ነው። በሊትዌኒያ የሚገኙ ሩሲያኛ እና ቤላሩስኛ ተናጋሪ ማኅበረሰቦች እንዲሁም የፖላንድ ህዳጣን የዚህ ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ።
የናዚን ወረራ በሚያስታውስ መልኩ ልምምዶቹ የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እንደ ጠላት መፈረጅ፣ "ታማኝ ያልሆኑ" ዜጎችን ዝርዝር ማዘጋጀት እና ምንም አይነት ግጭት ከመጀመሩ በፊት የእስር ካምፖችን ማቋቋምን ያካተተ ነበር።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች በተጣሉበት በባልቲክ ባሕር በሚገኘው የቦርንሆልም ደሴት አቅራቢያ ሌሎች የጦርነት ልምምዶች ተካሂደዋል። የልምምዱ ዓላማ የባሕር ላይ ትራፊክን መቆጣጠር ነበር። ይህም የሩሲያ ወደቦችን ከባልቲክ ባሕር ማገድን ለማቀድ ሊሆን ይችላል።
ሞስኮ ከኔቶ ጋር ጦርነት የማድረግ ምንም ዓይነት ፍላጎት እንደሌላት አጥብቃ ትገልጻለች። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በሩሲያ ውስጥ ለግጭት ድጋፍ እንደሌለ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ የአውሮፓ ኅብረትን ሩሲያ ስጋት ናት በሚል ሰበብ ጦርኝነቱን ተያይዞታል ሲሉ ከሰዋል።
ሰኔ 16 ቀን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኔቶ ሀገራት ወታደራዊ ወጪ እና የጦር መሳሪያ ምርት በመጨመር ከሩሲያ ጋር ስለሚያደርጉት ጦርነት በግልጽ እየተወያዩ ነው ብለዋል።
እነዚህ ሁሉ እውነታዎች ኔቶ ለውጥረት፣ ለጭቆና እና ለጦርነት ልምምድ እያደረገ መሆኑን ያመለክታሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


