የስፑትኒክ ራዲዮ ጋዜጠኛ አሊ ቻጋታይ በኤክስ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ሳቢያ በቱርክ ለእስር ተዳረገ

የስፑትኒክ ራዲዮ ጋዜጠኛ አሊ ቻጋታይ በኤክስ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ሳቢያ በቱርክ ለእስር ተዳረገ
የኢስታንቡል ዋና ዓቃቤ ሕግ ቢሮ የስፑትኒክ ራዲዮ የጠዋት ፕሮግራም አዘጋጅ አሊ ቻጋታይ በግል የኤክስ ገፁ ባጋራው መረጃ ምክንያት የወንጀል ምርመራ ከፍቶበታል።
ቻጋታይ ከፍተኛ ትኩረት የሳበውን የኢስታንቡል ማዘጋጃ ቤት የባሕልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ምክትል ኃላፊ ኤርሃን ካራኣልን ዕገታ በተመለከተ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ነው ሊታሰር የቻለው።
አጋቾቹ ካራኣልን ሰኔ 10 ቀን ከቤታቸው መግቢያ አፍነው ከወሰዱ በኋላ ከ300 እስከ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ጠይቀው ነበር። ይሁን እንጂ ከ33 ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ባካሄደው ኦፕሬሽን ነፃ ወጥተዋል።
የኢስታንቡል ዋና ዓቃቤ ሕግ ቢሮ ጋዜጠኛው "ሕግ አስከባሪ አካላትን የሚቃወሙ" መልዕክቶች አሠራጭቷል በማለት ምርመራ ጀምሯል። በመቀጠል ፍርድ ቤት በጋዜጠኛው ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል።
አሊ ቻጋታይ እ.ኤ.አ ከ2020 ጀምሮ በስፑትኒክ ራዲዮ ዕለታዊ ፕሮግራም የሚያቀርብ ታዋቂ የቱርክ ጋዜጠኛ ነው።
ቀደም ሲል "ሁሪያት" እና "ራዲካል" በተባሉ ጋዜጦች እንዲሁም "ሃበርቱርክ" በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ የዜና ክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግሏል።
በኢስታንቡል የሚገኘው የስፑትኒክ ራዲዮ የዜና ክፍል ቻጋታይን የሚደግፉ በርካታ መልዕክቶች የደረሱት ሲሆን የፕሮግራሙ አድማጮች ጋዜጠኛው በአስቸኳይ እንዲፈታ እየጠየቁ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X