ዚምባብዌ ለ500 ሜጋ ዋት በውሃ ተንሳፋፊ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ400 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቧ ተገለፀ

ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ ለ500 ሜጋ ዋት በውሃ ተንሳፋፊ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ400 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቧ ተገለፀ

​ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ "በግሪን ሃይብሪድ ፓወር" የሚመራውና በአፍሪካ ኢምፖርት-ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) የሚደገፈው ይህ ፕሮጀክት የሚከተሉትን ያካትታል፦

​▪ በውሃ ተንሳፋኢ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣
▪ የባትሪ ኃይል ማከማቻ፣
▪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች።

ይህ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፦

​▪ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፣
▪ የሥራ ዕድል መፍጠር፣
▪ ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ ለሚሸጋገሩ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ማድረግ።

​ የካሪባ ሐይቅን 0.2 በመቶ የሚሸፍነው ተንሳፋፊ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ፤ ከአካባቢው የዓሣ ማጥመድ፣ የቱሪዝም እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በተጓዳኝ ይሠራል።

​ የዚምባብዌ ዕለታዊ የኃይል ማመንጨት አቅም 1,500–1,800 ሜጋ ዋት ሲሆን ይህም ከከፍተኛው የፍላጎት መጠን 2,200 ሜጋ ዋት ያነሰ በመሆኑ መንግሥት እ.ኤ.አ በ2030 የታዳሽ ኃይል አቅሙን 2,100 ሜጋ ዋት ለማድረስ ግብ አስቀምጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0