ሶማሊያ በ1.4 ሚሊዮን ዶላር የተገነባውን የግብርና ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አስመረቀች

ሰብስክራይብ

ሶማሊያ በ1.4 ሚሊዮን ዶላር የተገነባውን የግብርና ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አስመረቀች

​በሶማሊያ የምግብ ሥርዓቶች መቋቋም ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የተገነባውና አዲሱ ዘመናዊ ባለ አራት ፎቅ ሕንፃ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትሩ መመረቁን የግብርና ሚኒስትር ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

ሕንጻው፤ "ለልማት፣ ለግልጽነት እና ጥራት ላለው የማኅበረሰብ አገልግሎት ማረጋገጫ ሆኖ የሚቆም ነው" ሲል መግለጫው አክሏል።

​ አዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት "ከልማት፣ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ለሶማሊያ ገበሬዎች እስካሁን ከተሰጡ ወይም በቅርቡ ከሚሰጡ በርካታ አገልግሎቶች" ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ተግባራትን የማስፋፋት አላማ እንዳለው የግብርና ሚኒስትሩ መሐመድ አብዲ ሃይር ማሬዬ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0