አዲሱ በመረጃ የተደገፈ የድንበር እና የኤርፖርት ሥርዓት የኢትዮጵያን የደኅንነት አቅም ያሳድጋል - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

© telegram sputnik_ethiopiaአዲሱ በመረጃ የተደገፈ የድንበር እና የኤርፖርት ሥርዓት የኢትዮጵያን የደኅንነት አቅም ያሳድጋል - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
አዲሱ በመረጃ የተደገፈ የድንበር እና የኤርፖርት ሥርዓት የኢትዮጵያን የደኅንነት አቅም ያሳድጋል - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.06.2026
ሰብስክራይብ

አዲሱ በመረጃ የተደገፈ የድንበር እና የኤርፖርት ሥርዓት የኢትዮጵያን የደኅንነት አቅም ያሳድጋል - የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

 

ይህ የተገለጸው የተቀናጀ የኤርፖርት እና የድንበር አስተዳደር ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ዐቢይ ኮሚቴ የምክክርና የግብዓት ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

 

ተነሳሽነቱ የላቁ የመረጃ መረብ መሣሪያዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ውስብስብ እና ተለዋዋጭ የደኅንነት ስጋቶች በብቃት ለመመከት የሚያስችል እንደሆነ፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

ይህ የተቀናጀ ሥርዓት በዋናነት፦

▪ሽብርተኝነት፣

▪የሰዎች ዝውውር፣

▪የገንዘብ ማጭበርበር፣

▪ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን የመሳሰሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ያለመ ነው።

ለዚህ ስትራቴጂካዊ ሽግግር ስኬታማነት የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የሎጂስቲክስ ሥርዓቶች እንዲሁም አስፈላጊ የአሠራርና የሕግ ማዕቀፎችን ያካተተ ዝርዝር የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አስቀድሞ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0