የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ

ሰብስክራይብ

የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ

87.6 ሄክታር መሬት የሚሸፍነው እና 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ፕሮጀክክቱ በዛሬው ዕለት በይፋ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

ይህ ሰፊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎችን በጋራ ያያዘ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

"ፕሮጀክቱ የግንባታ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ መዲናችንን የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋምና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች፣ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስልታዊ ሽግግር የሚያፋጥን ታላቅ አጋጣሚ ነው።" ብለዋል፡፡

ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተሰጣቸውን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎችን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመሩት ጉዞ አበክረው እንደሚቀጥሉበት ቃል ገብተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0