42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን ውድድር በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ
17:54 28.06.2026 (የተሻሻለ: 18:04 28.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን ውድድር በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ውድድር፤ ዛሬ እሁድ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት ከቀኑ 5:00 ሠዓት በኋላ ነበር የተጀመረው፡፡
ውድድሩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለክልል ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለክለቦችና ለግል የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑ ፌዴሬሽኑ ቀደም ሲል ገልጿል።
አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታት ዓላማ ተደርጎ መዘጋጀቱ የተገለጸው ሲሆን 74 ሴት፣ 249 ወንድ በድምሩ 323 አትሌቶች ተሳትፈዋል።
በውድድሩ ከ1-3 ለወጡ እና በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አንጋፋ አትሌቶች ከሜዳሊያ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia