ኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን በብሪክስ አባል አገራት መካከል ጠንካራ የጠፈር ትብብር እንዲኖር ጥሪ አቀረበች
15:39 28.06.2026 (የተሻሻለ: 15:44 28.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
🪐 ኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን በብሪክስ አባል አገራት መካከል ጠንካራ የጠፈር ትብብር እንዲኖር ጥሪ አቀረበች
በሕንድ ቤንጋሉሩ በተካሄደው የብሪክስ የጠፈር ትብብር ስብሰባ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፤ በአባል አገራቱ መካከል በጠፈር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ጥልቅ አጋርነት መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
ይህ ዓይነቱ ትብብር ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን፣ የአደጋ ስጋት አመራርን ለማሻሻልና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ብቸኛው የሥነ-ፈለክ ምልከታ ማዕከል የሆነው የእንጦጦ አስትሮኖሚካል ኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ በዘርፉ እያደረገች ያለውን መስፋፋት ልዑኩ አብራርቷል።
የብሪክስ የጠፈር ምክር ቤት እንዲቋቋም ኢትዮጵያ ሙሉ ድጋፏን የገለጸች ሲሆን፤ አዳዲስ አገራት በብሪክስ የርቀት ዳሰሳ ሳተላይት ጥምረት ውስጥ እንዲካተቱ ጠይቃለች።
በሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባጋራው መረጃ መሠረት፤ በብሪክስ አገራት መካከል በጠፈር ዳታ መጋራት፣ በአቅም ግንባታ፣ በጋራ የሳተላይት ተልዕኮዎች እና የጠፈር ፍርስራሾችን በመቀነስ ረገድ የላቀ ትብብር እንዲኖር ጥሪ ቀርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia