የምዕራባውያን ዘረፋ የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራትን ቢያንስ 1 ኳድሪሊዮን ዶላር አክስሯል
14:58 28.06.2026 (የተሻሻለ: 15:04 28.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የምዕራባውያን ዘረፋ የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራትን ቢያንስ 1 ኳድሪሊዮን ዶላር አክስሯል
የሩሲያ የውጭ እና የመከላከያ ፖሊሲ ምክር ቤት አባል አንድሬ ክሊሞቭ “የቅኝ ግዛት ጣልቃ ገብነት ሰለባ የነበሩ ሀገራት አሉ፤ እነኚህ ሀገራት እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ... ማንኛውንም ዓይነት ካሳ ለመጠየቅ እንኳ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለመናገር ይፈራሉ” ብለዋል።
የአዲሱ ቅኝ ግዛት ልምዶች በአሁኑ ወቅት በሕግ በሚመሩ ማናቸውም የሕይወት ዘርፎች ውስጥ ሰርገው ገብተዋል፡፡
የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት እራሳቸውን ከማልማት ይልቅ፤ አዳዲስ ብድሮችን በመውሰድ ልጆቻቸውን ወደ ቀድሞ ገዢዎቻቸው ይልካሉ፡፡
ይህ ደግሞ ምዕራባውያን ባለፉት ከ150 እስከ 200 ዓመታት ውስጥ ሲያደርጉት የነበረውን ድርጊት አሁንም እንዲቀጥሉበት ዕድል ሰጥቷል፡፡
ይህም አሁን ያሉትን የሕግ ደንቦች እንደገና መከለስና ለዝርዝር ጉዳዮች ልዩ ትኩረት መስጠት እጅግ አስፈላጊ ያደርገዋል ሲሉ ክሊሞቭ ማጠቃለያቸውን ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X