የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ሥራዎችንና አዲስ የተቋቋመውን የፈረሰኛ ፖሊስ መምሪያ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ይህ አዲስ አደረጃጀት ተቋሙ እያካሄደው ያለው ሁለንተናዊ የሪፎርም ሥራ ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፤ አዲስ ሥራ የጀመረው የፈረሰኛ ፖሊስ ክፍል 300 መደበኛ ፖሊሶች ሊሸፍኑት የሚችሉትን የጸጥታና የወንጀል መከላከል ሥራ በአንድ ፈረሰኛ ፖሊስ ብቻ ለመሸፈን የሚያስችል በመሆኑ ለተቋሙ ትልቅ ተጨማሪ አቅም ነው ብለዋል።

በማዕከላዊ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ መምሪያ ደረጃውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ እንዲሁም የስቲምና ሳውና ባዝ አገልግሎቶች ተገንብተው ለአባላት ተላልፈዋል።

ከፌደራል ፖሊስ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተገኘ ቆየት ያለ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ አዲስ ያደራጀውን የፈረሰኛ ፖሊስ ዋና ክፍል በይፋ ሥራ አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0