በኢትዮጵያ ዓመታዊ የዲጂታል ግብይት 24.2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የዲጂታል ግብይት 24.2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ኢትዮጵያ ከተበታተኑና ከተነጠሉ አሠራሮች ወደ ተቀናጀ የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማት የምታደርገው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሽግግር ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ይገኛል ሲል ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።

ቀደም ሲል በውል የማይታወቅና ግልጽ ያልነበረው ዓመታዊ የዲጂታል ግብይት መጠን ያስመዘገበው ዕድገት፤ ለፖሊሲ አውጪዎች ግልጽነትን በመፍጠር የታለሙ የፋይናንስ እርምጃዎችን ለመውሰድ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ተብሏል።

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ የተመዘገቡ 4 ቁልፍ ስኬቶች

🟠 የዲጂታል ግብይት ሥርዓት፦ ዓመታዊ የዲጂታል ግብይት መጠን ከማይታወቅበት ደረጃ ተነስቶ አሁን ላይ 24.2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።

🟠  የቴሌኮም ደንበኞች ምዝገባ፦ የተመዝጋቢ የደንበኞች ቁጥር ከ37.9 ሚሊዮን ወደ 85 ሚሊዮን በላይ ያደገ ሲሆን፤ ይህም ለዲጂታል ትስስርና ለገበያ ተሳትፎ ዋነኛ መሠረት ሆኗል።

🟠 የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፦ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም የገበያ ምዝገባ እና የማረጋገጫ ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

🟠 የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ፦ ፕሮግራሙ ከተጀመረ ወዲህ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰልጣኞች ትምህርታቸውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብን የዲጂታል አቅም በከፍተኛ ደረጃ ገንብቷል።

ይህ አጠቃላይ የተቀናጀ የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር ግንባታ የአገሪቱን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማት ይበልጥ እያዘመነውና ወደ መዋቅራዊ ሽግግር እየመራው መሆኑ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0