ኢትዮጵያ በ5 ዓመታት ውስጥ ከቡና ወጪ ንግድ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የሚያስችላትን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ አደረገች
12:34 28.06.2026 (የተሻሻለ: 12:44 28.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ5 ዓመታት ውስጥ ከቡና ወጪ ንግድ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የሚያስችላትን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ አደረገች
በቀጣዮቹ 5 ዓመታት የሚተገበረው አዲሱ “ሀገራዊ የቡና ልማት ፓኬጅ” ከቡና የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ አሁን ካለበት 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ያለመ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።
በስትራቴጂው በዘርፉ ያለውን ዘልማዳዊ አሠራር በመቀየር፣ አሁን በሄክታር 9 ኩንታል የሆነውን የቡና ምርት መጠን ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ ታቅዷል።
በዚህም የአየር ንብረት ለውጥና በሽታን የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ አዳዲስ የቡና ዝርያዎችን ለገበሬዎች በስፋት ለማሰራጨት በጂማ የግብርና ምርምር ማዕከል እየተገነባ ያለው የቲሹ ካልቸር ማዕከል ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
በተጨማሪም ምርታማነትን ለማሻሻል 50 በመቶ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) እና 50 በመቶ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያን ቀላቅሎ ለመጠቀም የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X