ሩሲያ አዳዲስ ገበያዎች ላይ በማተኮር ወደ አፍሪካ እና ሌሎች ቀጣናዎች የወጪ ንግዷን እያሰፋች ነው - ባለሥልጣን
11:59 28.06.2026 (የተሻሻለ: 12:04 28.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ አዳዲስ ገበያዎች ላይ በማተኮር ወደ አፍሪካ እና ሌሎች ቀጣናዎች የወጪ ንግዷን እያሰፋች ነው - ባለሥልጣን
ሞስኮ ቀደም ሲል በሩሲያ አምራቾች ዘንድ ይታወቁ ወዳልነበሩ ሀገራት የወጪ ንግዷን እየገነባች ሲሆን፤ አፍሪካ፣ ደቡብ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ተስፋ ሰጪ ቀጣናዎች ተብለው መለየታቸውን የኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስቴር የመንግሥት ዋና ጸሐፊና ምክትል ኃላፊ ሮማን ቼኩሾቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እንደ እሳቸው ከሆነ፤ እነዚህ ገበያዎች እንደ አፍሪካ ያሉ አጠቃላይ ቀጣናዎችን ያካልላሉ፤ አልያም ደግሞ ወደ ሦስተኛ ሀገራት ገበያ ለመድረስ የሚያስችሉ ዐቢይ የወጪ ንግድ መልሶ መላኪያ ማዕከላት ሆነው ያገለግላሉ።
የሩሲያን የወጪ ንግድ ለማሳደግ የተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎች፦
የነጻ ንግድ ስምምነቶች
የጋራ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶች
በላኪዎች እና በልማት ተቋማት መካከል የተቀናጀ ሥራ
እነዚህ እርምጃዎች ተሰናስለው የሩሲያ ምርቶች በውጭ አገር ገበያዎች ላይ ያላቸውን ተደራሽነት ያሳድጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቼኩሾቭ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X