የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርገው መመራት አለባቸው - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል

የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ህ
የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ህ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.06.2026
ሰብስክራይብ
የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርገው መመራት አለባቸው - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል

በሞስኮ “የመጪው ጊዜ ፍልስፍና፤ ሃሳቦችና ፍቺዎች” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ዓለም አቀፍ የሳይንስ ኮንፈረንስ ላይ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያዊው የፓርላማ አባል በሞስኮ የሳይንስ ኮንፈረንስ ላይ ታዳጊ የአፍሪካ ሀገራት ለዘላቂ ሰላምና ለቀጣናዊ ትስስር ሲሉ ሳይንሳዊ ምርምሮችንና የፖሊሲ ቀረጻዎችን ከውጭ ተጽዕኖ ነፃ በሆነ መንገድ ሊመሩ እንደሚገባ አጎልተው አንስተዋል።

የቴክኖሎጂ አምራችነት በጥቂት ሀገራት እጅ መውደቁ በታዳጊ ሀገራት ላይ አደጋ እንዳይፈጥር ሥጋት መኖሩ በኮንፍረንሱ የተገለጸ ሲሆን፤ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት የመረጃ ደኅንነታቸውን እና የዲጂታል ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ጠንካራ የሕግና የተቋማት መዋቅር መገንባት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በርካታ አዋጆችን በማፅደቅ ለሀገራዊ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ግንባታ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ያስታወሱት ዶ/ር ፈትሂ፤ በቀጣይም በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የተገኙ የላቁ ሳይንሳዊና የፖሊሲ ተሞክሮዎችን በመቀመር የምክር ቤቱን የክትትልና ቁጥጥር ሚና ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

ይህ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤ በሰው ሰራሽ አስተውሎቶ፣ በሳይበር ደኅንነት እና በቴክኖሎጂ ጂኦፖለቲካዊ ሽግግሮች ዙሪያ ሰፊ የምሁራን ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርገው መመራት አለባቸው - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርገው መመራት አለባቸው - የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0